የአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የፅዳት ዘመቻ አካሄዱ

65

አዲስ አበባ፤ የካቲት 27/2012(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክር አብይ አህመድን ጨምሮ የአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የጽዳት ዘመቻ ላይ ተሳተፉ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በአዲስ አበባ የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል።

ዛሬ ማለዳ ከ4 ሺህ በላይ የፓርቲው አመራሮች በከተማዋ ፅዳት ከማካሄድ በተጨማሪ የተተከሉ ችግኞችንም ተንከባክበዋል።

ዘመቻው "ቆሻሻ አስተሳሰብንና ቆሻሻን ከከተማዬ አጸዳለሁ" በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደ መሆኑም ታውቋል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ስልጠና ላይ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም