የህዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ 8100A መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የህዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ 8100A መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ
አዲስ፤ አበባ የካቲት 25/2012 (ኢዜአ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ 3ኛውን ዙር በ8100 የአጭር የፅሁፍ መልእክት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በይፋ አስጀመሩ፡፡
ፕሬዝዳት ሳህለወርቅ ለህዳሴ ግድብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ 3ኛ ዙር የ8100A አጭር ፅሁፍ መልእክት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብርን ይፋ አድርገዋል።
በኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲጠናቀቅ የህዝቡ ተጨማሪ ድጋፍ አስፈላጊ በመሆኑ የገቢ ማሰባሰቢያው ይፋ ሆኗል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም ከ70 በመቶ በላይ መድረሱ ይታወቃል።