ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ዱራሜ ገብተዋል

65

አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2012 ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዱራሜ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በዱራሜ ስታዲየም ለተሰበሰቡት በሽዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ከደቂቃዎች በኋላ ንግግር ያደርጋሉ።

ከሰአት በኋላ ደግሞ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ ማለዳ ዱራሜ ሲገቡ በአካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም