በአፋር ክልል የኢንዱስትሪ ፓርክ ሊገነባ ነው

4
አፋር ሰኔ 21/2010 በአፋር ክልል ለሚገነባው የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ በዛሬው እለት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ። በሰመራ ከተማ የሚገነባው የኢንዱስትሪ ፓርክ አንድ ሺህ ሔክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን ለመጀመሪያ ዙር ግንባታው 200 ሔክታር መሬት መዘጋጀቱም ተገልጿል። በአገሪቱ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደተገነቡና በመገንባት ላይ እንዳሉ ይታወቃል። ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በቀጣይም እስከ አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ለማስፋት መታቀዱን በፓርኩ ምረቃ ወቅት መነገሩ ይታወሳል። ሁለተኛው ምዕራፍ የኢንዱስትሪ ፓርኩ ማስፋፊያ ደሴን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ አካባቢዎችን የሚያካትት የኢንቨስትመንት ኮሪደር ልማት ጥናትን መሰረት በማድረግ እንደሚከናወንም ነው የጠቆሙት። የመቐለ ኢንዱስትሪያል ፓርክ 15 ሼዶች ያሉት ሲሆን 100 ሄክታር መሬት ላይ አርፎ ይገኛል፡፡ በ100 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው የኢንዱስትሪ ፓርኩ በአሁኑ ሰአት ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በመሆን ወደ ስራ መግባት የሚችሉ ባለሀብቶችን ከውጪና ከአገር ውስጥ በመመልመል ላይ ይገኛል። በተያያዘ የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም