የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተጀመረ

91
ጅጅጋ  የካቲት 15 /2012  (ኢዜአ) ሁለት ሺህ 500 መካከለኛ አመራሮች የሚሳተፉበት የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ስልጠና ዛሬ በጅግጅጋ፣ ጎዴና ዶሎ አዶ ከተሞች ተጀምሯል። በጅግጅጋ ከተማ ዛሬ የተጀመረው ስልጠና ከፋፈን፣ ፊቅ፣ ደጋህቡርና ሲቲ ዞኖች በሚገኙ ወረዳዎችና ከተሞች የተውጣጡና በቅርቡ በአዳማ ከተማ በተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ያልተሳተፉ  አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል ። ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር መሐመድ ሻሌ እንደገለፁት ስልጠናው ሀገራዊና ክልላዊ የለውጥ ስራዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስቀጠል ይረዳል። "የስልጠናው ዋና ዓላማ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ መካከለኛ አመራሮች የአመለካከትና የተግባር አንድነት እንዲኖራቸው ለማስቻል መሆኑን ገልፀዋል ። የፓርቲው  አመራሮች በሁሉም መስክ ያላቸውን የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ ስልጠናው የላቀ ጠቀሜታ እንደሚኖረው  ኢንጅነሩ ተናግረዋል ። ብልፅግና ፓርቲ ሀገራዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ባስቀመጣቸውን ስትራቴጂክ እቅዶችና የፓለቲካ ፕሮግራሙ ላይ መካከለኛ  አመራሮች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑንም ከኢንጂነር መሀመድ ገለፃ ለማወቅ ተችሏል ። ስልጠናው ለቀጣይ አስራ አምስት ቀናት እንደሚቆይ ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችለዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም