በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስጊድ አካባቢ ባሉ ሱቆች የእሳት አደጋ ተከሰተ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስጊድ አካባቢ ባሉ ሱቆች የእሳት አደጋ ተከሰተ
አዲስ አበባ ሰኔ 21/2010 በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስጊድ የሴቶች መግቢያ አካባቢ ባሉ ሱቆች የእሳት አደጋ ደርሷል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሪፖርተር በቦታው ደርሶ እንዳስተዋለው በመስጊዱ ዙሪያ በራጉኤል ቤተክርስቲያን በኩልና በፊትለፊት በባቡር መስመሩ በኩል የነበሩ የኤሌክትሮኒክስ ሱቆች ወድመዋል። ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ጀምሮ የተነሳው ቃጠሎውን ለማጥፋት በአዲስ አበባ የሚገኙ ስምንቱ የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች እና ከአየር መንገድ ድጋፍ ተጠይቆ በተደረገው ርብርብ እሳቱ ወደ ንጋት አካባቢ መቆጣጠር መቻሉን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠር ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል። እንደ አቶ ንጋቱ ገለጻ የወደመው ንብረት መጠንና የእሳቱ መንስኤ በማጣራት ላይ ነው።