በሃዋሳ ከተማ ለውጡንና የብልጽግና ጉዞን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሔደ ነው

69

ሃዋሳ፤የካቲት 13/2012 (ኢዜአ) በደቡብ ክልል በሃዋሳ ከተማና አካባቢዋ የሚገኙ የሲዳማ ብሔር ተወካዮችና የከተማዋ ነዋሪዎች የብልጽግና ጉዞውን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሔዱ ነው።

የተለያዩ መልዕክቶችን የያዙ ሰልፈኞች በሃዋሳ ስታዲየም በመገኘት በሃገሪቱ እየመጣ ያለውን የብልጽግና ጉዞ እንደሚደግፉ እየገለጹ ይገኛሉ።

ዛሬ ማለዳ 12 ሰዓት በጀመረው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ከሲዳማ አስተዳደርና ከ36 ወረዳዎች የተውጣጡ የሲዳማ ብሄር ተወካዮች፣ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችና የመንግስት ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም