ቀጥታ፡

ቦይንግ 737 አውሮፕላን የነዳጅ ቱቦ ውስጥ ስብርባሪ ተገኘ

የካቲት 11/2012 (አዜአ) ቦይንግ 737 አውሮፕላን የነዳጅ ቱቦ ውስጥ ስብርባሪ መገኘቱ ተሰማ፡፡ ቦይንግ 737 አውሮፕላን በአለፈው አመት መጋቢት ወር ላይ  ለሶስት መቶ አርባ ስድስት ሰዎች ህይወት ማለፍ  ምክንያት ከሆነ በኋላ በርካታ አየር መንገዶች አውሮፕላኑን ከበረራ ማገዳቸው እና በቦይንግ ዙሪያ  በርካታ የጠርጣሬ ዜናዎች መነበባቸውን ቀጥሏል፡፡ አሁን ደግሞ ቦይንግ 737 አውሮፕላን የነዳጅ ቱቦ ውስጥ አላስፈላጊ ስብርባሪ መገኘቱ አሁንም የቦይንግን አውሮፕላን አሳሳቢነት ከፍ አድርጎታል፡፡ ተገኘ የተባለው ስብርባሪ  የአውሮፕላኑ ሰራተኞች በአውሮፕላኑ የነዳጅ ቱቦ ውሥጥ የረሷቸው አላስፈላጊ ብረታብረት እንዲሁም ከጥቅም ውጪ የሆኑ ቁርጥራጮች ተብሏል፡፡ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን መረሃ ገብር ዋና ስራ አስኪያጅ ጀምስ ጄንክ ለቦይንግ ሰራተኞች ይህ ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ነው  ደርጅቱ  በቅርቡ ወደበረራ ይመለሳል ብለዋል፡፡ የቦይንግ ቃል አቀባይ በበኩላቸው   የሁኔታውን ትክክለኛነት  እያረጋገጥን ነው፤ ሆኖም ይህ አጋጣሚ ለአውሮፕላኑ አገልግሎት መጀመር እንቅፋት ሊሆን አይችልም ብለዋል፡፡ (ቢቢስ)
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም