ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከተውጣጡ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

የካቲት 5/2012(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከተውጣጡ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ተወካዮች ጋር ተወያዩ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ ልዩ ልዩ ሀገራት ኑሯቸውን ካደረጉ ኢትዮጵያውያን የተውጣጡ 300 የማኅበረሰብ ተወካይ እና አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል። ተወያዮቹ ስለ ወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ፣ በየሚኖሩባቸው ሀገራት የአምልኮ ስፍራዎችን እና ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችሉ ቦታዎችን ስለ ማግኘት፣ እንዲሁም ሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮችና ችግሮቻቸውን ለውይይት ያቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ምላሽ ሰጥተውባቸዋል። አቡዳቢ ሲደርሱም የአገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼህ አብዱላሂ ቢን ዛይድ አል-ናህያን አቀባበል አድርገውላቸዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም