ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አቀኑ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አቀኑ
የካቲት 5/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዛሬ አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚያደርጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ከ15 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ትናንት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መግለጻቸው ይታወቃል። በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሚኖሩና ከመካከለኛው ምስራቅ ከመጡ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይት እንደሚያደርጉ ነው አቶ ንጉሱ የገለጹት። የኢትዮጵያ መንግስት በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ዜጎች መብታቸው እንዲከበር የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል። በአገር ውስጥ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ጀምሮ በሚኖሩበት አገር የሚገጥማቸውን ችግር ለመፍታት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አቶ ንጉሱ ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከየካቲት 5 እስከ 7 ጉብኝት ያደርጋሉ።