ዓለም አቀፉ የእርሻ ልማት ፈንድ  ለሞዛምቢክ 43 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

156
ኢዜአ የካቲት  3/2012 ዓለም አቀፉ የእርሻ ልማት ፈንድ (ኢፋድ) ለ 88 ሺ ሞዛምቢካውያን አነስተኛ አሳ አርቢዎች የ43 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ፡፡ ለአሳ ምርት ምቹ የሆነ የአየር ሁኔታ አላት የምትባለው ሞዛምቢክ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዳትሆን  የገንዘብ፣የቁሳቁስ  እጥረት  እቅፋት መሆናቸው በምክንያት ተጠቅሷል፡፡ በዋናነት አነስተኛ የገጠር አሳ አምራቾችን ለማገዝ  ይፋ የተደረገው የገንዘብ ድጋፉ፣ የአሳ ምርቱ ከነበረበት አነስተኛ ደረጃ  ወደ ህብረት ስራና ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገባ ለማስቻል መሆኑም ተገልጿል፡፡ ግንባር ቀደም  የድጋፉ ተጠቃሚዎች ሴቶችና ወጣቶች ሲሆኑ ፕሮጀክቱ በሚያሳካቸው ቀጣይ ግቦች የአገሪቱ መንግስት ድህንትን ለመቀነስ ለሚያደርገው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ ዋና አጋዥ እንደሚሆንም ታምኖበታል፡፡ ከድጋፉ ውስጥ 8.6 ሚሊዮን ዶላሩ በብድር መልክ ሲሆን የቀረው 34.4 ሚለዮን ዶላር ደግሞ በእርዳታ መልኩ እንደተሠጠ አፍሪካን ቢዝነስ አስነብቧል፡፡ ኢፋድ በሞዛምቢክ እ.ኤ.አ ከ1993 ጀምሮ ባደረገው ከ386 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ከ2ሚሊን በላይ በገጠር የሚኖሩ ሞዛምቢካውያን ተጠቃሚ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም