ቀጥታ፡

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ የኢትዮጵያ ቆይታቸውን አጠናቀቁ

አዲስ አበባ የካቲት 02/2012 ( ኢዜአ) የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሴኔጋል አምርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፣ ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከሌሎችም የስራ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል። ከተለያዩ ኢትዮጵያዊያን የስራ ፈጣሪዎች እና ባለሃብቶች ጋር መወያየታቸውም ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ሴኔጋልን ለመጎብኘት በነበራቸው  እቅድ  በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ቆይታቸውን አጠናቀው  ወደ  ሰኔጋል አምርተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አሸኛኘት አድርገውላቸዋል። ኢትዮጵያና የካናዳ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት እንደ አውሮጳዊያን አቆጣጠር ከ1965 ጀምሮ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም