የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ የካቲት 01 /2012 ( ኢዜአ ) የአፍሪካ ህብረት 33ኛው የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ አዲስ አበባ በሚገኘው የህብረቱ ዋና መስሪያ ቤት መካሄድ ጀመረ። ለቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጓል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በመክፈቻው ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ ያለፈው አመት በርካታ ችግሮች ያጋጠሙበት ቢሆንም የተመዘገቡ ድሎች ነበሩ። የጎርፍ አደጋና የአንበጣ መንጋ ተከስቶ ጉዳት ማድረሱ ባለፈው አመት ካጋጠሙ ችግሮች ውስጥ እንደ ነበሩ ተናግረዋል። የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት፣ በሶማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል እንዲቀጥል ማድረግ፣ እንዲሁም ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ስራዎች ውጤት የመጣበት እንደ ነበር አስታውሰዋል። በሱዳን የተደረገው ሽግግር ለአፍሪካውያን የተመዘገበ ስኬት እንደ ነበር ለአብነት አንስተዋል። ይህ የተጀመረው ዓመት አጋርነትን በማጠናከር በተለያዩ መስኮች የተሻለ ውጤት የሚመዘገብበት እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ አንድነት መስራች አባቶች ህልም የነበረው አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና እውን የሚሆንበት ዓመት እንደሚሆን ተናግረዋል። የዓመቱ መሪ ሃሳብ የሆነው ጸጥታና ሰላምን ለማስጠበቅ የጦር መሳሪያ ድምጽን ማጥፋት አፍሪካ ማሸነፍ የምትችልበት ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ገልጸዋል። በመድረኩ ተጋብዘው ንግግር ያደረጉት የአረብ ሊግ ዋና ጸሐፊ አህመድ አብዱል-ጌይት በበኩላቸው የዓመቱ መሪ ሃሳብ ከአረብ ሊግ አገሮች አቋም ጋር የሚሄድ መሆኑን ገልጸው፤ ውጤት ለማምጣት በጋራ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል። ሰላምን ለማምጣትና ሽብርተኝነትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ሊጉ የሚደግፍ መሆኑን ጠቁመዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ ባደረጉት ንግግር ተመድ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ እንዲሁም የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ከህብረቱ ጋር ተባብሮ የሚሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በጤና፣ በትምህርት፣ በመሰረተ ልማትና በተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ለመሆን ተመድ ትብብር የሚያደርግ መሆኑን አመልክተዋል። ሙስናን መዋጋት፣ የታክስ ስርዓትን መከለስና ሃብትን በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል ተገቢነት እንዳለው ገልጸዋል። የጾታ እኩልነትን ማረጋገጥና የሴቶችን አቅም ማጎልበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በተመሳሳይ ወጣቱን ተጠቃሚና ተሳታፊ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ አስረድተዋል። ለአየር ንብረት ለውጥ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል በትብብር መሰራት እንዳለበትም ገልጸው፤ በሊቢያ ያለውን ቀውስ በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት ማንኛውም አካል ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠብ ጠይቀዋል። የፍልስጤም ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ በፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ ሽታይን በኩል ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ላገኙት የሰላም የኖቤል ሽልማት የተሰማቸውን ገልጸው፤ ሽልማቱ ኢትዮጵያ ለሰላም የምታደርገውን ጥረት ያሳያል ብለዋል። የአፍሪካ አገሮች ለፍልስጤም ያላቸውን አጋርነት አድንቀዋል። ሰላምና ጸጥታ ማስከበር እንዲሁም ሽብርተኝነትን መዋጋት ለዓለም ዓቀፉ ህግ መገዛትን የሚጠይቅ መሆኑን አስገንዝበዋል። የህብረቱ ተሰናባች ሊቀመንበር የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ግብጽ ሊቀመንበር በነበረችበት አንድ አመት የነበረው ትብብር አዎንታዊ ውጤት ማምጣት ማስቻሉን ጠቁመዋል።
በአመቱ ያጋጠሙትን ችግሮች ለመፍታት አፍሪካዊ መፍትሄ ለአፍሪካ ችግሮች በሚለው መርህ መሰረት በመሰራቱ ስኬት ማስመዝገብ መቻሉን ጠቁመዋል። በተለይም በአህጉሩ በተለያዩ አካባቢዎችና አገሮች የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት ማገዙን ተናግረዋል። በሰላምና ጸጥታ፣ በአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና፣ በኢኮኖሚ መተሳሰር፣ በመሰረተ ልማትና በሌሎች መዋቅራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል። ለሚቀጥለው አንድ አመት የህብረቱ ሊቀመንበር ሆነው የሚያገለግሉት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የተጣለባቸውን ሃላፊነት በደቡብ አፍሪካ ህዝብ ስም መቀበላቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነው፤ ከዚህ ቀደም እ.አ.አ በ2002 በቀድሞው ፕሬዚዳንት ታቦ ምቤኪ የአስተዳደር ዘመን ደቡብ አፍሪካ ህብረቱን በሊቀመንበርነት መምራቷን አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት መሆኗን በስፋት ያነሱት ፕሬዚዳንት ራማፎሳ የአፍሪካ ህብረት መስራች አባቶችን ህልም እውን ለማድረግ በትትብር መስራት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። አፍሪካ በተፈጥሮ ሃብት የታደለች ብትሆንም ከድህነት መውጣት አለመቻሉን ተናግረው፤ ድህነት እርግማን ባለመሆኑ አጀንዳ 2063 በማሳካት ከድህት መውጣት የሚቻልበት ዕድል መኖሩን ተናግረዋል። ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በመለየት ለስኬት መስራትና ዘላቂ የልማት ግቦችን እውን ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል። የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና መርሃ ግብር እውን ሊሆን የሚችለው መሰረተ ልማትን በማስፋፋት በመሆኑ ለመሰረተ ልማት ግንባታ ትኩረት በመስጠት የሚሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ዲጂታል ቴክኖሎጂን በማስፋፋት ተወዳዳሪ መሆን እንደሚገባ በመጠቆም። የሴቶችን የገንዘብና ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና ተሳታፊነት በማረጋገጥ፣ የጾታ ጥቃትን በመከላከል ለአፍሪካ እድገት መስራት የሚያስፈልግ መሆኑን አስገንዝበዋል። በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታን እውን ለማድረግ ከተመድና ከሌሎች ዓለም ዓቀፍ አካላት ጋር በመሆን በተለያዩ አገሮች ያለውን ግጭት ለመፍታት እንደሚሰራ ተናግረዋል። የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመገንባት የጦር መሳሪያችንን እናስቀምጥ ያሉት ፕሬዚዳንት ራማፎሳ፤አፍሪካ የውክልና ጦርነት አውድማ መሆኗ ማብቃት እንዳለበት ገልጸዋል።