የምርጫ አስፈፃሚዎች ከፖለቲካ ተሳትፎ ነጻና ገለልተኛ እንዲሆኑ ይሰራል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ - ኢዜአ አማርኛ
የምርጫ አስፈፃሚዎች ከፖለቲካ ተሳትፎ ነጻና ገለልተኛ እንዲሆኑ ይሰራል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 30/2012 የምርጫ አስፈጻሚዎች ከፖለቲካ ተሳትፎ ነጻና ገለልተኛ እንዲሆኑ ከተፎካካሪ ፓርቲዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚሰራ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቦርዱ ለአገር አቀፉ ምርጫ ከ250 ሺህ በላይ አስፈጻሚዎችን ለመመልመል ከወዲሁ ዝግጅት እያደረገ ነው። ለምርጫው በመላ አገሪቷ ከ48 ሺህ 500 በላይ ምርጫ ጣቢያዎች ይኖራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በእያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያም እስከ አምስት አስፈጻሚ እንደሚያስፈልግ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባል ወይዘሮ ብዙወርቅ ክተት ለኢዜአ እንዳሉት መጪውን ምርጫ ፍትሃዊ፣ ተአማኒና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የአስፈጻሚዎች ምልመላ አካሔድ ዋነኛው ነው።
በመሆኑም ቦርዱ እነዚህን አስፈጻሚዎች ለመመልመል የምርጫ ህጉ በሚያዘው መሰረት በመስፈርቶቹ ላይ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በመመካከር እንደሚሰራ ተናግረዋል። ቀደም ሲል ምርጫ አስፈጻሚዎች በወረዳ አስተዳደር በኩሉ ይጠቆሙ እንደነበር ያስታወሱት ወይዘሮ ብዙወርቅ "በዘንድሮ ምርጫ ይህን አሰራር ለመቀየር እየሰራን ነው" ብለዋል። ማስታወቂያ በማውጣት የምርጫ ክልል ኃላፊዎች ቅጥር መፈጸሙን ገልጸው ይህም ውድድርና ብቃትን መሰረት አድርጎ ከመከናወኑ ባለፈ የፖለቲካ ፓርቲዎችም አስተያየት እንደሰጡበት ጠቅሰዋል። እንደ ወይዘሮ ብዙወርቅ ገለጻ በቦርዱ በኩል የምርጫ አስፈጻሚዎችን የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ተመልምለው ስልጠና የሚወስዱበት መንገድ እየተመቻቸ ነው። አዲሱ የምርጫ ሕግ በሚያዘው መሰረት በአሁኑ ወቅት 79 ፓርቲዎች ዳግም ምዝገባ ማድረጋቸውን ገልጸው ከእነዚህ መካከል 32 በአገር አቀፍ ደረጃ፣ 47 ደግሞ በክልል ደረጃ የተመዘገቡ መሆናቸውን አመልክተዋል። ከዚህ በፊት አገልግሎት ላይ የዋሉ ምርጫ ጣቢያዎች ቁጥር፣ ስያሜና ቦታ እንዲሁም አሁን ያሉበት ሁኔታ ላይ እየተደረገ ያለው ጥናት እየጠተናቀቀ መሆኑንም ገልጸዋል። ከዚህ ጎን ለጎን እየተካሔደ ያለው አጠቃላይ ሪፎርም በቦርዱ ላይ ይነሱ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ምርጫውን በተሻለ ለማካሔድ የሚያግዝ መሆኑን አመልክተዋል።