የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩድ አዲስ አበባ ገቡ

80
ጥር 29/2012 (ኢዜአ) የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩድ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ማምሻውን አዲስ አበባ ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቱ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክሩ ነው የተገለጸው። የኢኮኖሚ አማራጮች፣ የአየር ንብረት ለውጥን በጋራ መከላከል፣ የዴሞክራሲና የሴቶች እኩልነት በውይይቱ የሚዳሰሱ ጉዳዮች እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ጋር በአገሪቷ አነስተኛ የወጭ ንግድ ማስፋፊያ ዓለም አቀፍ የንግድ ሚኒስትር  የተመራ ልዑክም ገብቷል። የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ከጎብኝታቸው በተጓዳኝ በአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ላይ እንደሚታደሙ ታውቋል። በተመሳሳይም የቦትስዋናው መሪ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል። የኢትዮጵያና የካናዳ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመረው እንደ አውሮጳዊያኑ የዘመን ቀመር ከ1965 ወዲህ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም