የጎብኚዎች አቀባበልና የጉብኝት ስራዎች በሰለጠኑ ባለሙያዎች ሊከናወኑ ይገባል - የቱሪዝም ባለሙያ - ኢዜአ አማርኛ
የጎብኚዎች አቀባበልና የጉብኝት ስራዎች በሰለጠኑ ባለሙያዎች ሊከናወኑ ይገባል - የቱሪዝም ባለሙያ
ጥር 29/2012 (ኢዜአ) ወደ አዲስ አበባ ከተማ ለተለያዩ ትላልቅ ኮንፍረንሶችና ጉብኝት የሚመጡ የውጭ እና የሀገር ውስጥ እንግዶችን አቀባበልና የጉብኝት ስራዎች በሰለጠኑ ባለሙያዎች ማከናወን እንደሚገባ በቱሪዝም ዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተናገሩ። በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የቱሪዝም መምህር አሉላ አክሊሉ ለኢዜአ እንደተናገሩት በመዲናዋ በኮንፍረንስ ቱሪዝም ዘርፉ ላይ የተሰማራው አብዛኛው የሰው ሀይል በልምድ እየሰራ ነው። የእንግዶችን አቀባበል፣ የትራንስፖርት ፣ የሆቴልና ሌሎች አገልግሎቶችን የማመቻቸት፣ የጉብኝትና የተለያዩ ኩነቶችን የማዘጋጀት ስራዎች በሰለጠነ የሰው ሀይል ሊከናወኑ እንደሚገባም ነው የገለጹት። ባለሙያዎቹ ወቅቱ ከሚጠይቀው ቴክኖሎጂዎች ፣ዕውቀትና ክህሎት ጋር የሚጣጣም አቅም ሊኖራቸው እንደሚገባም የጠቀሱት መምህር አሉላ፤ ይህም ከኮንፍረንስ ቱሪዝም ዘርፉ የሚገኘውን ገቢ በማሳደግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነው ያስረዱት። በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና ብቃት ማረጋገጥ ዳይሬክተር አቶ አምደማርያም ማሞ በበኩላቸው ቢሮው ከተለያዩ አካላት ጋር በመሆን በቱሪዝም ዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
የአቅም ግንባታ ሥራዎቹንም በስፋትና በተጠናከረ መንገድ ለማስቀጠልና ከቱሪዝም ኮንፍረንስ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግም የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። በመዲናዋ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሚመጡ እንግዶች የመዲናዋን የቱሪስት መስህቦች እንዲጎበኙ ለማድረግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ መውጫ በሮች ላይ የቱሪስት መስህቦች መረጃ የሚሰጡ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንዲተላለፉ እየተደረገ መሆኑንም ለአብነት አንስተዋል። የጎብኚዎች መመሪያ መጻህፍትና ብሮሸሮች በአየር መንገድ የማሰራጨት ስራ እየተሰራ መሆኑንና ጎብኚዎች በብዛት በሚያርፉባቸው አለም አቀፍ ሆቴሎች ላይም የመረጃ ዴስክ መቋቋሙን ጠቁመዋል። በአፍሪካ ህብረት ግቢ ውስጥ የመዲናዋን የቱሪስት መስህቦች የመረጃ ዴስክ ለማቋቋም ለተቋሙ ጥያቄ መቅረቡን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ በመዲናዋ ለጉብኝትና ለኮንፍረንስ የሚመጡ እንግዶች ደህንነት የተጠበቀ ለማድረግ ከጸጥታና ሌሎች አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። በአንዳንድ አገራት የጎብኚዎችን ደህንነት የሚጠብቁ ከመደበኛ ፖሊስ በተጨማሪ ‘የቱሪስት ፖሊሶች’ የመመደብ ልምድ መኖሩንም አንስተው፤ በቀጣይም ይህን ተሞክሮ ተግባራዊ የማድረግ እቅድ እንዳላቸውም አቶ አምደ ማርያም ጠቁመዋል። በአዲስ አበባ አርፈው ወደ ሌሎች አገራት የሚጓዙ መንገደኞች በመዲናዋ በሚኖራቸው ቆይታ የከተማዋን የቱሪስት መስህቦች እንዲጎበኙ ከአለም ባንክና ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑንም ነው የገለጹት።