ቀጥታ፡

አዲሱ የኅብረቱ የመዋቅር ሽግግር የሠራተኞችን መብት ከግምት ያስገባ መሆን አለበት

አዲስ አበባ፣ ጥር 28/2012(ኢዜአ) የአፍሪካ ኅብረት አዲሱ የመዋቅር ሽግግር ግልጽነትን ያረጋገጠና የሠራተኞችን መብት ከግምት ያስገባ መሆን አንዳለበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው አሳሰቡ። የኅብረቱ የመዋቅር ማሻሻያ የደረሰበትን ደረጀ በተመለከተ በተዘጋጀው ሪፖርት ላይ የአስፈጻሚ ምክር ቤቱ ተወያይቷል። የአባል አገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችም በቀረበው ሪፖርት ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስርትር ገዱ አንዳርጋቸው እንደተናገሩትም የኅብረቱ የመዋቅር ማሻሻያ በመሪዎች ጉባዔ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ግቡን እንዲመታ ግልጽነትን ባረጋገጠና የሠራተኞችን መብት ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ መከናወን አለበት። የኀብረቱ የሰው ኃይል አደረጃጀት መዋቅር ችሎታና ኃላፊነትን ግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሁም ልምድና ብቃትን ማዕከል ያደረገ መሆን አለበትም ብለዋል። ወደ አዲሱ መዋቅር የሚደረግ ሽግግር የሠራተኞችን መሰረታዊ መብትም ከግምት ያስገባ ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም