ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

161
አዲስ አበባ ሰኔ 19/2010 ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾመዋል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘይኑ ጀማል ለኢዜአ እንዳረጋገጡት፤ ሜጀር ጄነራል ደግፌ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዋል። ከዚህም በተጨማሪ ረዳት ፖሊስ ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ እና አቶ ዘላለም መንግስቴ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተደርገው መሾማቸውን ጠቁመዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም