ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የዲኒቅ ጨልጨል የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ስራን አስጀመሩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የዲኒቅ ጨልጨል የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ስራን አስጀመሩ
አዲስ አበባ ጥር 26/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዲኒቅ ጨልጨል የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ስራ በይፋ አስጀመሩ፡፡ ባሌን በልማት ለመቀየር መንግስት የሚሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዲኒቅ ጨልጨል የመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ስራ በይፋ አስጀምረዋል፤ በተመሳሳይም የወልመል ወንዝ መስኖ ልማት ፕሮጀክትን በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል፡፡ በዛሬው ዕለት ስራው በይፋ የተጀመረው የዲኒቅ ጨልጨል የመስኖ ፕሮጀክት በባሌ ዞን ራይቱ ወረዳ በ4ሺ 146 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባ የመስኖ ፕሮጀክት ነው፡፡ የመስኖ ፕሮጀክቱ በ2015 ሲጠናቀቅ በራይቱ ወረዳ በ7 ቀበሌ የሚገኙ ከ8ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ የፕሮጀክቱ ባለቤት የፌደራል መንግስት ሲሆን ለግንባታውም ከ2 ቢሊየን 823 ብር በላይ ተመድቧል፡፡
በዚሁ ወቅት ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፤ ''ከአሁን በኋላ ዋነኛ ትኩረታችን ልማትን ማፋጠን እና ለወጣቱ ትውልድ የስራ ዕድል መፍጠር ነው'' ብለዋል፡፡ የፕሮጀክቱን ግንባታ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የሚያከናውነው ሲሆን የኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ደግሞ የማማከሩን ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡ የተመረቀው የወልመል መስኖ ፕሮጀክት በምዕራብ ባሌ ዞን በዶሎመና ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ከ400 ሄክታር በላይ መሬት የማልማት አቅም ያለው ነው፡፡ ይህ የመስኖ ፕሮጀክትም ከ1 ሺህ 123 በላይ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ ጀምሯል። ለፕሮጀክቱግንባታ 36 ሚሊዮን ብር ወጥቶበታል። ይህን ፕሮጀክት ያስመረቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለህዝቡ ባደረጉት ንግግር ''የወጣቱን እምቅ ሃይል ለልማት ብቻ እናውለዋል'' ብለዋል፡፡ የመጣው ለውጥ የህይወት መስዋዕትነት የሚፈልግ ትግል የሌለው መሆኑን ጠቁመው፤ አንድነትን በመጠበቅ ልማትን ማፋጠን እንደሚገባ አመልክተዋል። የወልመል መስኖ ልማት ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 11 ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት አቅም እንዳለውም ተገልጿል። ግንባታውን ባስጀመሩበት ወቅት ወጣቶች ከመንግስት ጎን ሆነው የአገሪቱን ልማት እንዲያፋጥኑ ጠይቀዋል። 4 ሺህ 114 ነጥብ 7 ሄክታር መሬትን ያለማል የተባለው የመስኖ ልማት ፕሮጀክቱ፤ በምስራቅ ባሌ ዞን የሚገኙ የራይቱ እና የጊኒር ወረዳ አርሶ አደሮችን እና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡ የውልወል ግድብ ግንባታ እና የመስኖ ልማት ፕሮጀክት በባሌ ዞን የሚገኝ ሲሆን፣ፕሮጀክቱ በራይቱ እና ጊኒር ወረዳዎች ያለውን የምግብ ዋስትና እና የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ አስተዋጽዖ ይኖረዋል።