የገናሌ ዳዋ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የገናሌ ዳዋ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመረቀ
ጥር 26/2012 (ኢዜአ) የገናሌ ዳዋ ቁጥር 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ተመርቋል። በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ተጋባዥ እንግዶችም ተገኝተዋል፡፡ 2003 ዓ.ም የተጀመረው ፕሮጀክቱ 254 ሜጋ ዋት የኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል። ግንባታው 9 ዓመታትን በመፍጀቱ ከተያዘለት ጊዜ ዘግይቶ የተጠናቀቀ ፕሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ 451 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጎበታል። የፕሮጀክቱ ሥራ መጀመር የሀገሪቱን ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅምን ወደ 4654 ሜ.ዋ ከፍ ያደርገዋል መባሊን የዘገበው ኢቢሲ ነው።