መንግስት በሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሮ እና ሀይድሮ መካኒካል ስራዎች በወሰደው አፋጣኝ እርምጃ ለውጥ ተመዝግቧል- ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ - ኢዜአ አማርኛ
መንግስት በሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሮ እና ሀይድሮ መካኒካል ስራዎች በወሰደው አፋጣኝ እርምጃ ለውጥ ተመዝግቧል- ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ
አዲስ አበባ ጥር 23/2012 (ኢዜአ) መንግስት በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሮ እና ሀይድሮ መካኒካል ስራዎች ላይ በወሰደው አፋጣኝ እርምጃ ትልቅ ለውጥ መመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዳሴውን ግድብ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል። ከጎብኝታቸው ጎን ለጎንም የሲቪል ምህንድስናና የኤሌክትሮ እና ሀይድሮ መካኒካል ስራውን ከሚያከናውኑ የውጭ ኩባንያ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአንድ ዓመት በፊት ፕሮጀክቱን በጎበኙበት ወቅት የኤሌክትሮ እና ሀይድሮ መካኒካል ስራዎቹ በሚፈለገው አግባብና ጥራት እየተከናወኑ እንዳልነበረ አስታውሰዋል። መንግስት በወሰደው ፈጣን የማስተካከያ እርምጃ በአንድ ዓመት ጊዜ የኤሌክትሮ እና ሀይድሮ መካኒካል ስራዎቹ በሚፈለገው ጥራትና የጊዜ ሰሌዳ እየተከናወኑ መሆኑን መገንዘባቸውንም ገልጸዋል። ከግድቡ 13 የኃይል ማመንጫ ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 እና 10 የመጀመሪያ ምዕራፍ የኃይል ማመንጨት ስራ በ2013 ዓ.ም እንደሚጀምሩም አመልክተዋል። መንግስት በግድቡ ግንባታ የታዩ መልካም ጎኖችን በማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም ግድቡ የቀጣዩ ትውልድ ሀብት እንዲሆን ይሰራል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ። ስህተቶችን ማረምና መልካም ነገሮችን ማስቀጠል የመደመር ፍልስፍና አካል እንደሆነም ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሕዳሴው ግድብ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ዶክተር አብይ ጥሪ አቅርበዋል። 'የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በጥራት መገንባት ጥቅሙ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ከታኛው ተፋስስ አገራት ጋር መተማመን የሚፈጥርልን ነው' ብለዋል። የሕዳሴው ግድብ አጠቃላይ የግንባታ አፈጻጸም 71 በመቶ የደረሰ ሲሆን በጣልያኑ የስራ ተቋራጭ ሳሊኒ ኢምፔርጂሎ የሚከናወነው የሲቪል ምህንድስና ስራ 86 በመቶ፣ የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው ደግሞ 35 በመቶ ላይ ይገኛል። የውጭ ኩባንያዎች የኤሌክትሮና ሀይድሮ መካኒካል ስራዎችን ከመረከባቸው በፊት ስራዎቹ ይከወኑ የነበሩት በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/ ነበር።