የፓኪስታን ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
የፓኪስታን ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ
ጥር 22/2012 (ኢዜአ) የፓኪስታን-አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤ ከጥር 20 እስከ 21/2012 በናይሮቢ ተካሂዷል። በጉባኤው ላይ በሲሚንቶ ምርት፣ በአገልግሎት፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በኬሚካል እና ሌሎችም መስኮች የተሰማሩ ባለሃብቶች ተሳትፈዋል።
በናይሮቢ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ኢትዮጵያ ቅድሚያ የምትሰጣቸው የኢንቨስትመንት አማራጮችን በተመለከተ ለተሳታፊዎቹ ገለፃ ማድረጋቸው ተጠቅሷል። በመድረኩ ላይ ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ተሳትፎ እያደረጉ ሲሆን ከፓኪስታን ባለሃብቶች ጋር የተናጠል ውይይት አምባሳደሩ ማድረጋቸውን በኬኒያ የኢትዮጵያ ኢንባሲ መረጃ ያሳያል፡፡