ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 22/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ የፊታችን ሰኞ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ። ምክር ቤቱ የፊታችን ሰኞ 1ኛ ልዩ ስብሰባ የሚያካሂድ መሆኑን ምክር ቤቱ ዛሬ ለኢዜአ የላከው መግለጫ አመልክቷል። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄና አስተያየቶች ምላሽ የሚሰጡ ይሆናል። ምክር ቤቱ በዕለቱ የ11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ቃለ ጉባኤ መርምሮ እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።