ቀጥታ፡

በአሜሪካና በሜክሶኮ ድንበር አቅራቢያ ረጅሙ የዕፅ ማዘዋወሪያ ዋሻ ተገኘ

ኢዜአ፤ ጥር 21/2012  በአሜሪካና በሜክሶኮ ድንበር አቅራቢያ ረጅሙን የዕፅ ማዘዋወሪያ ዋሻ ማግኘታቸውን የአሜሪካ ባለስልጣናት አስታወቁ።

1 ሺህ 313 ሜትር ርዝመትና ከመሬት በታች የ21 ሜትር ጥልቀት ያለው ዋሻው አሳንሰር (ሊፍት)፣ የባቡር ሀዲድ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ኤሌክትሪክ ሃይል መሸከም የሚችል መስመር እና አየር መቆጣጣሪያ መሳሪያ እንዳለውም ባለስልጣናቱ ገልጸዋል።

የመተላለፊያ ዋሻው የሜክሲኮን  ቲጁኣና ከተማ ከአሜሪካ ካሊፎርኒያ ከተማ ጋር የሚያገናኝ መሆኑ ተጠቅሷል።

የዋሻውን መግቢያ የሜክሲኮ ባለስልጣናት ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ ያገኙት ሲሆን ፤ በአሜሪካ የምርመራ ቡድንም የዋሻውን አጠቃላይ ይዞታ ተዘጋጅቶ በትናንትናው እለት ይፋ ሆኗል።

በዋሻው  ውስጥ የዕጽ ማዘዋወር እንቅስቃሴ የሚያካሂደውን አካል በተመለከተ በባለስልጣናት በኩል  መረጃ ያልተሰጠ ሲሆን  ምንም አይነት ዕጾችም አልተገኙም።

ሆኖም በአሜሪካ መንግስት እንደ አንድ ሜክሲኮ ዕጽ አዘዋዋሪ ቡድን የሚገለጸው  ‘ሲናሎኣ’ የተሰኘው ቡድን በአካባቢው እንደሚንቀሳቀስ ተመልክቷል።

በካሊፎርኒያና በሜክሲኮ ድንበር መካከል እ.ኤ.አ ከ2016 ጀምሮ ከደርዘን በላይ የሚደርሱ ውስብስብ የሆኑ ዋሻዎች መገኘታቸውን በዘገባው ተገልጿል።

ምንጭ: ቢ ቢ ሲ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም