የኮሮና ቫይረስ ምልክት የታየባቸው አራት ተጠርጣሪዎች መለየታቸውን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ

115
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጥር 19/2012 የኮሮና ቫይረስ ምልክት የታየባቸው አራት ተጠርጣሪዎች መለየታቸውን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ። ከተለዩት አራት ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሲሆን ሁለቱ ደግሞ ቫይረሱ በመጀመሪያ መከሰቱ ከታየበት ሁዋን ከተማ የመጡና በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ መሆናቸው ተገልጿል። ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በበሽታው የተጠረጠሩት ግለሰቦች በሽታው ባይገኝባቸውም ምልክቱ ስለታየባቸው ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው ነው። በአገር ውስጥ በተደረገ ምርመራ ነጻ መሆናቸው ቢረጋገጥም ሙሉ ለሙሉ ነጻ ስለመሆናቸው ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የደም ናሙናቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ መላኩን ሚኒስቴሩ ገልጿል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም