የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ጀመረ

66
መቀሌ፤ጥር 16/2012 የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአምስተኛ ዘመን 18ኛው ዙር መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ማካሄድ ጀመረ። በመቀሌ ከተማ ምክር ቤት አዳራሽ  የተጀመረው ጉባዔ ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት  እንደሚቆይ ተገልጿል። ምክር ቤቱ የክልሉ ሥራ አስፈጻሚ አካላትን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸምን ጨምሮ በ21 ረቂቅ ዓዋጆችና ጉዳዮች ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከነዚህ መካከልም ዳግም ወረዳዎችን ለማደራጀት የወጣውን ረቂቅ ዓዋጅ ጨምሮ የከተሞችና የወረዳዎች የስራ አፈጻጸምን፣ የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ረቂቅ ዓዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸድቅም  ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል። በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና በዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ላይም ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም