የአዲስ አበባ ምክር ቤት የስራ ኃላፊዎችን ሹመት አፀደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ አበባ ምክር ቤት የስራ ኃላፊዎችን ሹመት አፀደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በዛሬ መደበኛ ስብሰባው የ19 የስራ ኃላፊዎችን ሹመት አፀደቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሔደው 7ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ስብሰባው ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ያቀረቡትን የስራ ኃላፊዎች ሹመት ተቀብሎ አጽድቋል። የቀረበው ሹመት በ79 ድጋፍ፣ በ3 ተቃውሞ እና በ7 ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው። በዚሁ መሰረት፡- 1. ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ፡- በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ 2. ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠው፡- የቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ 3. ወይዘሮ ነጂባ አክመል፡- የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ 4. አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ፡- የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ 5. አቶ አብዱልቃድር መሀመድ፡- ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ 6. ወይዘሮ ኤፍራህ አሊ፡- የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ 7. አቶ ኃይሉ ሉሌ፡- የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ 8. አቶ ዘላለም ሙለታ፡- የትምህርት ቢሮ ኃላፊ 9. ኢንጂነር ደመላሽ ከበደ፡- የኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ 10. አቶ ስጦታው ታከለ፡- የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ 11. አቶ ነጋሽ ባጫ፡- የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ 12. አቶ ይመር ከበደ፡- የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ 13. አቶ መኮንን ተፈራ፡- የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ 14. አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ፡- የንግድ ቢሮ ኃላፊ 15. አቶ አዱኛ ደበላ፡- የሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ 16. አቶ አብርሃም ታደሰ፡- የወጣቶች በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ 17. አቶ ዋቁማ አበበ፡- የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር 18. አቶ ታምራት ዲላ፡- የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር 19. አቶ ታዜር ገብረእግዚአብሄር፡- የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል።