ባለፈው ቅዳሜ በነበረው የድጋፍ ጥቃት ያደረሱ ተጠርጣሪዎችን ለመለየት እየሰራሁ ነው-ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን

68
አዲስ አበባ ሰኔ 18/2010 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድን ለመደገፍ በተጠራው ሰልፍ ላይ የተፈጸመውን የቦንብ ጥቃት  የሚመረምር ቡድን ተዋቅሮ እንቀስቃሴ መጀመሩን የፌዴራል ፖሊሰ አስታወቀ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ዛሬ በሰጡት መግለጫ በቡድኑ ውስጥ የአሜሪካውን ፌዴራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ.ቢ.አይ)'ን ጨምሮ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንደዚሁም የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ተሳትፈውበታል። ቡድኑ በተቻለ መጠን ምርመራውን በፍጥነት አጠናቆ ውጤቱን ለሕዝብ እንደሚያሳውቅም ኮሚሽነር ጄኔራሉ አረጋግጠዋል። አያይዘውም የተለያዩ ሀገራትም በምርመራው ሂደት የየበኩላቸውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ማሳወቃቸውን ገልጸዋል። እስካሁን በድርጊቱ የተጠረጠሩ 28 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከነዚም መካከል በወቅቱ በፍተሻ ላይ የነበሩ አመራሮች እንደሚገኙበት አመልክተዋል። በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው ጥቃት አስካሁነ የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከ150 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደረሷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም