የዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ የቀድሞ ተቃናቃኛቸውን ለፓርቲ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ጋበዙ

79

ጥር 15/2012 የዩጋንዳው ፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ እና ገዥው ፓርቲ ናሽናል ሬዚዝታንስ ሙቭመንት የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትርና የፓርቲው ፀሃፊ የነበሩትን ጆን ፓትሪክ አማማ ምባባዚን በዚህ ሳምንት በሚካሄደው ሃገራዊ የገዥው ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ እንደገኙ መጋበዛቸውን ዘ-ኢስት አፍሪካ አስነበበ፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የወቅቱ ፖርቲ ፀሃፊ የነበሩት መባባዚ እ.አ.አ በ2016 በተካሄደው የሃገሪቱ ብሄራዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒን በመቃወም ከፓርቲው እንደወጡ ዘገባው አስታውሷል፡፡

ምባባዚም እ.አ.አ እስከ 2014 ከስራቸው እስኪባረሩ ድረስ የፕሬዚዳንት ሙሰቨኒ የቅርብ ሰውና ታማኝ ሚኒስትራቸውም እንደነበሩ ዘገባው አትቷል፡፡

የሃገሪቱ ብሄራዊ የምርጫ ኮሚሽን እ.አ.አ ከጥር 1986 ጀምሮ ስልጣን ላይ የሚገኘው የ75 ዓመቱን አዛውንት መሪ በ2021 ድጋሚ በሚካሄደው ምርጫ ይደግፋል ተብሎም እንደሚጠበቅም ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ሃገሪቱን ለ34 ዓመታት በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ናሽናል ሬዚዝታንስ ሙቭመንት ፓርቲ ብሄራዊ ክብረ ብዓሉን ከማክበሩ በፊት በናቦሌ ስታዲየም ህዝባዊ ኮንፈረንስ እንደሚያካሄድም በዘገባው ተገልፃል፡፡

ከሶስት ሳምንታት በፊት ፕሬዚደንት ሙሴቪኒ የእርሳቸውንና የቀድሞ ታማኝ ሚኒስትራቸው ኪሶሲ በተሰኘ የእርሻ ስፍራቸው ላይ የተነሱትን ፎቶ በትዊተር ገፃቸው ላይ ማጋራታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም