ለአህጉሪቱ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ተግባር በትኩረት መረባረብ ይገባል---ም/ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ

70
ኢዜአ ጥር 13/2012 የአፍሪካን ፈጣን ለውጥ እና ዕድገት ለማረጋገጥ ለአህጉሪቱ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ በትኩረት መረባረብ እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳስበዋል፡፡ በአፍሪካ ዕድገት ማዕቀፍ ውስጥ እ.ኤ.አ 2025 ዓ.ም በዋናነት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የሚያጎለብት ፕላትፎርም ተቋቁሟል። ዳቮስ በተዘጋጀው የአፍሪካ የዕድገት ፕላትፎርም መድረክ ላይ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና ትልልቅ የዓለምአቀፍ ኩባንያ ሃላፊዎች በጋራ መክረዋል። በመድረኩ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ለአህጉሪቱ ፈጣን ዕድገት በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ በትኩረት መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል። በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች በየዓመቱ የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው መንግሥት በትኩረት እየሰራ መሆኑን በማሳያነት መልካም ተሞክሮ አጋርተዋል። በቀጣይ የአፍሪካ የዕድገት ፕላትፎርም ከተቀመጠለት የጊዜ ወሰን አኳያ ሀገራት ስኬታማ ልምዶችን እና ውጤታማ ተሞክሮዎችን የሚጋሩበት መድረክ ሊፈጠር እንደሚገባ አስታውቀዋል። የአለም ኢኮኖሚክ ፎረም የአፍሪካ ምዕራፍ እ.ኤ.አ በመጪው መስከረም 2020 ዓ.ም አዲስ አበባ እንደሚካሄድ በመጠቆም፤ ለተሻለ ልምድ ልውውጥ መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ  መኮንን መጥቀሳቸውን  ከምክትል ጠቅላይ ጽ/ቤት ይፋዊ  ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳል ።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም