ቀጥታ፡

ጥምቀት በጅግጅጋ ተከበረ

ጅግጅጋ ጥር 11 ቀን 2012 በጅግጅጋ ከተማና አከባቢዋ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች የጥምቀት በዓል አከበሩ። ምዕመናኑ በዓሉን ያከበሩት ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ ነው፡፡ በከተማውና አካባቢው የሚገኙ ዐብያተ ክርስቲያን ትናንት በከተራ በዓል የወጡት ታቦታትን ወደ ማረፊያቸው በመመለስ በዓሉን ሲያከብሩ ውለዋል። የቤተ ክርስቲያኗ የሶማሌ አገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ቄስ ደረጀ በቀለ የከተማው የእስልምና  እምነት ተከታዮችና የአስተዳደር አካላት እንዲሁም የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ትብብር በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። የጥምቀት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ሳይንስና የባህልድርጅት( ዩኔስኮ) የዓለም የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ ዘንድሮ መመዝገቡ ይታወቃል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም