የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ውሳኔ መተላለፉ ኢትዮጵያ በአለም ላይ ስሟን ዳግም እንድታድስ ያግዛል - ኢዜአ አማርኛ
የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ውሳኔ መተላለፉ ኢትዮጵያ በአለም ላይ ስሟን ዳግም እንድታድስ ያግዛል
ጥር 10/2012 (ኢዜአ) የጥምቀት በዓል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ ውሳኔ መተላለፉ ኢትዮጵያ በአለም ላይ ስሟን ዳግም እንድታድስ እንደሚያግዝ በአዲስ አበባ የከተራ በዓል ታዳሚዎች ገለጹ። ኢዜአ ያነጋገራቸው የበዓሉ ታዳሚዎች እንደገለጹት፤ የበዓሉ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ውሳኔ መተላለፉ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ለማስተዋወቅ ይረዳል። ዘንድሮ ዩኔስኮ በኮሎምቢያ ቦጎታ ባካሄደው ስብሰባ የጥምቀት በዓል የማይዳሰስ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ውሳኔ መተላለፉ ይታወቃል። ኢዜአ ያነጋገረው የከተራ በዓል ታዳሚ ወጣት ጌትነት ወርቁ በዓሉ በቅርስነት እንዲመዘገብ ውሳኔ መተላለፉ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ ባለቤት መሆኗን ለማስተዋወቅ እንደሚረዳ ገልጿል።
ወደ ኢትዮጵያ በርካታ ቱሪስቶች እንዲመጡ መንገድ የሚከፍት መሆኑንም ተናግሯል። ወጣት አለማየሁ ንጉሴ በበኩሉ በዓሉ አገሪቱ በችግር የምትነሳበትን ታሪክ በመቀየር የተለየ ገጽታ ለማላበስ እንደሚችል ተናግሯል።
በመሆኑም እንደ ጥምቀት ያሉ በዓላት በአለም ጎልተው መታየት መቻላቸው አገሪቱ ስሟን ዳግም እንድታድስና ገናና እንድትሆን ይበልጥ የሚያደርግ ነው ሲል ይገልጻል ። በዓሉ ህዝብ ለህዝብ ከማቀራረብና ይበልጥ ባህሉንም እንዲያስተዋውቅ ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም ተናግሯል። ''በመሆኑም ኢትዮጵያ ገና ብዙ ያልተጠቀመችባቸው በርካታ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ ቅርሶች ያሏት በመሆኗ ይህንንም ለአለም ህዝብ ይበልጥ የማስተዋወቅ ስራ መስራት ያስፈልጋል'' ብሏል። አገሪቱ ካላት የተፈጥሮና የታሪክ ሃብቶች አኳያም መጠቀም የሚገባትን ያህል ጥቅም እንዳልተጠቀመችም የከተራ በዓሉ ታዳሚዎች ገልጸዋል። የጥምቀት በአል በዩኔስኮ የተመዘገበ 4ኛው የማይዳሰስ ቅርስ ይሆናል ከዚህ ቀደም የመስቀል፣ የገዳ ስርዓትና ፍቼ ጨምበላላ በማይዳሰሱ የዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ መሆኑ ይታወቃል። ኢትዮያ እስካሁን ድረስ 13 ቅርሶቿን በዩኔስኮ በሚዳሰሱና በማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ያስመዘገበች ሲሆን፤ ዘጠኙ የሚዳሰሱ አራቱ ደግሞ የማይዳሰሱ የሰው ልጆች ወካይ ቅርስ ናቸው። በዚህም ኢትዮያ በአፍሪካ ውስጥ ከሚገኙ አገሮች ከ10 በላይ ቅርሶችን ያስመዘገበች ቀዳሚ አገር መሆኗን መረጃዎች ይጠቁማሉ።