የ15ኛ ሳምንት የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ትናትና ዛሬ ተካሄደዋል - ኢዜአ አማርኛ
የ15ኛ ሳምንት የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ትናትና ዛሬ ተካሄደዋል
አዲስ አበባ ሰኔ 18/2010 የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ትናትና ዛሬ በክልል ከተሞችና በአዲስ አበባ ተካሄደዋል። ትናንት ቡታጅራ ላይ መቀሌ ከተማ ቡታጅራ ከተማን 32 ለ 20 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ፤ ከትናንት በስቲያ ዱራሜ ላይ ከምባታ ዱራሜ ድሬዳዋ ከተማን 26 ለ 18 ረቷል። ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፌዴራል ፖሊስን 20 ለ 19 ማሸንፍ ችሏል። ነገ በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም የሊጉ መሪ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከፌዴራል ማረሚያ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። የ16ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየምና በክልል ከተሞች እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የሶስት ሳምንታት መርሃ ግብር ቀርተውታል። በኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ዘጠኝ ቡድኖች እየተሳተፉ ይገኛል።