ቀጥታ፡

ስሁል ሽሬ ፋሲል ከነማን አሸነፈ

መቐለ ጥር 8 / 2012  (ኢዜአ)  በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ዛሬ መቐለ ላይ በተካሄደ ጨዋታ ስሁል ሽረ ፋሲል ከነማን ሁለት ለባዶ አሸነፈ። በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም በተካሄደው ግጥሚያ ስሁል ሽረ  በ86ኛ ደቂቃ  ሳሊፎ ፎፎና  በ90ኛው ደቂቃ ደግሞ በመሐመድ አብደል ለጢፍ  ባስቆጠራቸው ግቦች ሙሉ ነጥብ ይዞ ወጥቷል። ክለቡ ውጤቱን ተከትሎ ከፋሲል ከነማ በ15 ነጥብ  ላይ ተቀምጧል። የፋሲል  ከነማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ  እንደገለጹት ተጋጣ ሚያቸው  በጥሩ ሁኔታ በመጫወቱ አሸንፏል።በቀጣይ ክፍተቶቹ  ለማስተካከል እንደሚሰራም ተናግረዋል። ደጋፊዎችና ተጫዋቾች ያሳዩት ስፖርታዊ ጨዋነትም ፍቅርና አንድነት የሚያንፀባርቅ እንደነበር አሰልጣኙ ገልጸዋል። የስሁል ሽረ አሰልጣኝ ሳምሶን አየነ በበኩላቸው ውጤቱን ''ጥሩ ተጫውተን ያስመዘገብነው ድል ነው'' ብለውታል። የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ለፋሲል ከነማ እግር ኳስ  ክለብ  ተጫዋቾችና ደጋፊዎች ትናንት የራት ግብዣ አድርጎላቸዋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግን  መቐለ 70 እንደርታ በ16 ነጥብ እየመራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም