የ2012 ሀገራዊ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የ2012 ሀገራዊ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፤ ጥር 6/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዘንድሮ አገራዊ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
ቦርዱ ዘንድሮ የሚካሄደውን ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ያዘጋጀውን የጊዜ ሰሌዳ ለሚመለከታቸው አካላት አቅርቦ ውይይት እያደረገበት ይገኛል።
በዚሁ መሰረት የምርጫ 2012 ዋና ዋና ቀናትና ተግባራት ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ሲሆን፤ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ምርጫ ነሐሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንዲሆን ሀሳብ ቀርቧል።
በዚሁ መሰረት ምርጫው ከተካሄደ ከነሐሴ 11 እስከ 20 ቀን 2012 ዓ.ም የቦርዱ የተረጋገጠ ውጤት ማሳወቂያ ጊዜ እንዲሆን በጊዜ ሰሌዳው ላይ ቦርዱ አቅርቧል።