የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር የኤርታሌ እሳተ ጎመራ ስፍራን ጎበኙ

ኢዜአ ጥር 5 1/ 2012 በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር በአፋር ክልል የሚገኘውን የኤርታሌ እሳተ ጎመራ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራን ጎበኙ። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር በአፋር ክልል የሚገኘውን የኤርታሌ እሳተ ጎመራ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራን ዛሬ ጎበኙ። አምባሳደሩ ጉብኝቱን ያካሄዱት በክልሉ የሚገኙ የመስህብ ስፍራዎች ያሉበትን ሁኔታ በማወቅ ለሀገራቸው ዜጎችና ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ ባላቸው ፍላጎት መሆኑን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ከሎይታ ለኢዜአ ተናግረዋል። የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባና የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከአምባሳደር ራይነር ጋር በጉብኝቱ ተካፍለዋል። አምባሳደር ራይነር በክልሉ የሚገኙ ዳሎልን ጨምሮ ሌሎች የቱሪስት መስህቦችንም እንደሚጎበኙ ኃላፊው አመልክተዋል። ኤርታሌ በአፋር ክልል ዞን ሁለት (ኪልባቲ ረሱ) የሚገኝ ሲሆን፣ "ኤርታ አሌ" የሚለው የአፋርኛ ቃል ትርጉምም "የሚጨስ ተራራ" ማለት ነው። ኤርታሌ የበርካቶች ቱሪስቶችና ሳይንቲስቶችን ቀልብ የሳበ የመስህብ ስፍራ መሆኑ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም