ሀድያ ሆሳዕና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲን በማሸነፍ ነጥቡን አሻሻለ - ኢዜአ አማርኛ
ሀድያ ሆሳዕና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲን በማሸነፍ ነጥቡን አሻሻለ
ኢዜአ ጥር 3/2012 በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲዮም ዛሬ በተካሄደው ስምንተኛው ሳምነት የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲን አንድ ለባዶ አሸነፈ። ሀድያ ሆሳዕና ክለብ የአሸናፊነቱን ግብ ያስቆጠረው ቢስማርክ ኦፖንግ በተባለው ተጫዋቹ አማካኝነት በ33ኛ ደቂቃ ነው። በዚህም ክለቡ ከነበረው አምስት ነጥብ ወደ ስምንት ከፍ በማድረግ ማሻሻል ችሏል። የወልዋሎ ዓድግራት ዩኒቨርስቲ ክለብ ተጫዋቾች ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም ግብ ማስቆጠር አልቻሉም። ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ የሀድያ የሆሳዕና ክለብ አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ በሰጠው አስተያየት " በጨዋታ ወልዋሎ ቢበልጠንም ከባለፉት ጋር ሰነጻጸር ግን አሁን ጥሩ ተጫውተናል "ብሏል። የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ክለብ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህለ በበኩሉ "በአጨራረስ ችግር ምክንያት ተሸንፈናል " ሲል ገልጿል።