8ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በተለያዩ ስታዲየሞች ይደረጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
8ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በተለያዩ ስታዲየሞች ይደረጋሉ
ኢዜአ ጥር 1/2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ይካሄዳሉ። የ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በተያዘላቸው መርሃ ግብር መሰረት እየተካሄዱ ይገኛሉ።
በዚህ ሳምንት ሰበታ ከተማ ከጅማ አባ ጅፋር ነገ ከቀኑ 9:00 ሰአት በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሀዲያ ሆሳዕና፣ ወላይታ ድቻ ከስሁልሽረ፣ ወልቂጤ ከተማ ከመቀለ ሰብአ እንደርታ፣ አዳማ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ፣ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከባህርዳር ከተማ እሁድ በተመሳሳይ በ9:00 ሰአት ክልል ላይ ይጫወታሉ።
እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከድሬደዋ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ፕሪሚየር ሊጉን ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ 14 ነጥብ ሲመራ፤ መቀለ ሰብአ እንደርታ በ13፣ ፋሲል ከነማ በ12 እንዲሁም ባህርዳር ከተማ በ11 ነጥብ ከ2 እስከ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ድሬዳዋ ከነማ፣ ወላይታ ዲቻ እና ሃዲያ ሆሳዕና ደግሞ ከ14 እስከ 16 ደረጃ ላይ በመያዝ በሊጉ ግርጌ ተቀምጠዋል።
ኮከብ ግብ አግቢነቱን የፋሲል ከነማው ሙጂብ ቃሲም በ6 ጎሎች እየመራ ይገኛል።
እንዳለ ከበደ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ማማዱ ሲዲቤ እና ፍጹም አለሙ ከባህር ዳር ከተማ፣ ብሩክ በየነ ከሃዋሳ ከተማ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከመቀለ ሰብአ እንደርታ እንዲሁም አዲስ ግደይ ከሲዳማ ቡና በእኩል 4 ጎሎች ይከተላሉ።