ቀጥታ፡

ከ170 በላይ ተጓዦችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው ቦይንግ 737 አውሮፕላን ተከሰከሰ

ኢዜአ፤ ታህሳስ 29/2012 ንብረትነቱ የዩክሬን አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ከ170 በላይ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ኢራን ውስጥ ዛሬ ማለዳ ተከስክሷል።

ከኢራን ቀይ ጨረቃ ማህበር በተገኘው መረጃ መሰረት በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት 176 መንገደኞች እና የበረራ ሰራተኞች ሁሉም ህይወታቸው አልፏል።

ከቴህራን የኢማም ክሆሜኒ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ወደ ኬቭ መብረር እንደጀመረ በቅርብ ርቀት ላይ መከስከሱን የፋርስ ኒውስ ኤጄንሲ በዘገባው ጠቅሷል።

የአደጋው ምክንያት እየተጣራ መሆኑን አልጄዚራ ና ቢቢሲ ዘግበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም