ቀጥታ፡

በታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የአምስተኛ ቀን ውሎ ስምንት የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል

ታህሳስ 24/2012.. በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በአምስተኛ ቀን ውሎው ስምንት የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል። ከ18 ዓመት በታች ሴት 200 ሜትር አትሌት የአብስራ ጃርሶ ከደቡብ ክልል 24 ሴኮንድ ከ7 ማይክሮ ሴኮንድ ስታሸንፍ አትሌት ፀጋ ቢዛና ከኦሮሚያ ክልል 26 ሴኮንድ ከ 00 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ ወጥታለች። የደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ተወዳዳሪዋ አትሌት ወይናገር ደረጀ 26 ሴኮንድ ከ 6 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች። ከ18 ዓመት በታች ወንድ 200 ሜትር አትሌት መሐሪ አለማየሁ ከደቡብ ክልል በ22 ሴኮንድ ከ59 ማይክሮ ሴኮንድ አሸናፊ ሲሆን አትሌት ጅብሪል ከሐረሪ ክልል 23 ሴኮንድ ከ7 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ ወጥቷል። ሌላኛው የደቡብ ክልል ተወዳዳሪ አትሌት ቃሲም ተማም በ23 ሴኮንድ ከ27 ሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ውድደሩን አጠናቋል። ከ18 ዓመት በታች ወንድ የሶስት ሺህ ሜትር ውድድር የደብረብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል። አትሌት ዳዊት ሀብቴ 8 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ ከ1 ማይክሮ ሴኮንድ አሸናፊ ሲሆን አልኣዛር ተፈራ 8 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ ከ4 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ ወጥቷል። አትሌት ቢምረው አወቀ 8 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ ከ7 ሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ከ18 ዓመት በታች ወንድ 1 ሺህ 500 ሜትር የደብረብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ተወዳዳሪ አትሌት እሸቱ መልኣክ 3 ደቂቃ ከ56 ሴኮንድ ከ5 ማይክሮ ሴኮንድ አሸንፏል። ሌላኛዋ የደብረብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ተወዳዳሪ አትሌት እንዳሻው ረታ 3 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ1 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ፣ አትሌት ሰኚ ፍቃዱ 4 ደቂቃ ከ00 ሴኮንድ ከ3 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ ወጥቷል። ከ18 ዓመት በታች ወንድ ከፍታ ዝላይ ሳምሶን ቤከማ ከኦሮሚያ ክልል 1 ነጥብ 85 ሜትር በመዝለል አሸናፊ ሲሆን የጋምቤላ ክልሉ ተወዳዳሪ አትሌት ኡድል ድድሙ 1 ነጥብ 80 ሜትር በመዝለል ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። አትሌት ቱዲስክ ሞግዳ ከደቡብ ክልል 1 ነጥብ 75  ሜትር በመዝለል ሶስተኛ ወጥቷል። ከ18 ዓመት በታች ሴት ስሉስ ዝላይ አትሌት አዲሴ አለሙ ከደብረብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 11 ሜትር በመዝለል አሸናፊ ሆናለች። አትሌት አስቴር ቶሎሳ ከኦሮሚያ ክልል 10 ነጥብ 50 ሜትር በመዝለል ሁለተኛ ሌላኛዋ የደብረብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ተወዳዳሪ አትሌት ትዕግስት ብርሃኑ 10 ነጥብ 46 ሜትር በመዝለል ሶስተኛ ወጥታለች። ከ16 ዓመት በታች ወንድ ስሉስ ዝላይ አትሌት ክብሮም ሀፍቱ ከትግራይ ክልል 12 ነጥብ 44 ሜትር በመዝለል አሸናፊ ሲሆን አትሌት ጨራ ታዬ ከኦሮሚያ ክልል 12 ነጥብ 22 ሜትር በመዝለል ሁለተኛ ወጥቷል። ሌላኛው የትግራይ ክልል ተወዳዳሪ አትሌት ሀብታሙ ታመነ 11 ነጥብ 17 ሜትር በመዝለል ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል። ከ16 ዓመት በታች ሴት የጦር ውርወራ አትሌት ማርታ ፋሪስ ከደቡብ ክልል 38 ነጥብ 17 ሜትር በመወርወር አሸናፊ ስትሆን አትሌት ደበሌ ዮናታን ከኦሮሚያ ክልል 35 ነጥብ 06 ሜትር በመወርወር ሁለተኛ ወጥታለች። የትግራይ ክልሏ ተወዳዳሪ አትሌት አኸዛ ተስፋዬ 21 ነጥብ 86 ሜትር በመወርወር ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ውድድሯን አጠናቃለች። ከፍጻሜ ውድድሮቹ በተጨማሪ ከ16 ዓመት በታች በሁለቱም ጾታዎች በተመሳሳይ የ200 ሜትር ማጣሪያ ውድድሮች ተካሄደዋል። ከታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአሰላ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ይጠናቀቃል። በሻምፒዮናው መዝጊያ ቀን ሰባት የፍጻሜ ውድድሮች እንደሚካሄዱም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም