ፊፋ 21 ኢትዮጵያውያን ዳኞች ዓለም ዓቀፍ ጨዋታዎችን የሚያጫውቱበት ባጅ ሰጠ - ኢዜአ አማርኛ
ፊፋ 21 ኢትዮጵያውያን ዳኞች ዓለም ዓቀፍ ጨዋታዎችን የሚያጫውቱበት ባጅ ሰጠ
ኢዜአ ታህሳስ 24 /2012 እ.አ.አ በ2020 ዓለም ዓቀፍ ውድድሮችን ለማጫወት የሚያስችል ባጅ ለ21 ዳኞች የዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ዛሬ ሰጠ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ባጁን ለተመረጡት ዳኞች አበርክተዋል። በዚሁ መሰረት ለሰባት ወንድ ዋና ዳኛ፣ ለስድስት ረዳት ወንድ ዳኛ፣ ለአራት ሴት ዋና ዳኛ እና ለአራት ረዳት ሴት ዳኛ ባጁ ተሰጥቷል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት የዓለም ዓቀፍ ዳኝነት ባጅ በፊፋ የተሰጣቸው ዳኞች ቁጥር 22 እንደነበሩ ይታወሳል። እ.አ.አ በ2020 ዓለም ዓቀፍ ውድድሮችን ለማጫወት የሚያስችል ባጅ ለ21 ዳኞች የዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ዛሬ ሰጠ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ባጁን ለተመረጡት ዳኞች አበርክተዋል። በዚሁ መሰረት ለሰባት ወንድ ዋና ዳኛ፣ ለስድስት ረዳት ወንድ ዳኛ፣ ለአራት ሴት ዋና ዳኛ እና ለአራት ረዳት ሴት ዳኛ ባጁ ተሰጥቷል። ባለፈው የፈረንጆች ዓመት የዓለም ዓቀፍ ዳኝነት ባጅ በፊፋ የተሰጣቸው ዳኞች ቁጥር 22 እንደነበሩ ይታወሳል።