ቀጥታ፡

የሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማስፋፊያ ግንባታ ባለመጠናቀቁ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ችግር እየፈጠረ ነው

ኢዜአ ታህሳስ 23/2012 የሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማስፋፊያ ግንባታ ባለመጠናቀቁ የኮሌጁን የመማር ማስተማር ሥራ ከማስተጓጎል ባለፈ በአከባቢዉ ነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል፡፡ የማህበረሰቡን ቅሬታ በተመለከተ ተጠይቆ አግባብ መሆኑን ያመነው የወላይታ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ በበኩሉ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረኩ ነኝ ብሏል፡፡ በኮሌጁ የአይሲቲ ትምህርት ክፍል 2ኛ ዓመት ተማሪ ሙሉቀን አበበ ከመማሪያ ክፍል ጥበት የተነሳ ብዙ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች በአንድ ክፍል ለመማር እንደሚገደዱ ተናግረዋል፡፡ በተለይም የከሰዓት ፈረቃ ከሙቀት የተነሳ ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዳይከታተሉ ማነቆ እንደሆነባቸው ነው የገለጸው፡፡ ሌላኛው አስተያየቱን የሰጡት በኮሌጁ የኮንስትራክሽን ማኔጅሜንት ትምህርት ክፍል መምህር ተመስገን ማሪዮ ተቋሙ ወደ ፖሊነት ሲያድግ በቴክኖሎጂ ዕውቀት የበለጸገና ዘመኑ የሚፈልገዉን የሰዉ ሃይል በማፍራት ለአከባቢውም ሆነ ለሃገር ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበት እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ለዚህም ኮሌጁ በስፋት የመማር ማስተማር ሥራውን ለማካሄድ የማስፋፊያ ስራዎች ቢጀመርም ባለመጠናቀቁ ይህን ታሳቢ በማድረግ የተገዙ የስልጠና ማሽነሪዎች ለጸሐይና ለብርድ በመጋለጣቸው ለጉዳት ከመዳረጋቸው በላይ ሥራቸውን በአግባቡ እንዳይሠሩ ተግደሮት እንደሆነባቸው አብራርተዋል፡፡ ከገጠማቸዉ የክፍል ጥበት የተነሳ ያሏቸዉን ተማሪዎች በቀን እስከ አራት ፈረቃ በመከፋፈል እያስተማሩ መሆናቸዉን ገልፀው ይህም ሊማሩ ከሚገባቸዉ ዝቅተኛዉን እንኳን ማሟላት አለመቻላቸውን ገልፀዋል፡፡ የዘርፉ የትምህርት አሰጣጡ 30 በመቶ በንድፈ ሃሳብና 70 በመቶ በተግባር እንዲማሩ የሚያስገድድ ሲሆን ይህን ማድረግ ባለመቻላቸዉ ብቁና ተወዳዳሪ የሰዉ ሃይል ከማፍራት ረገድ የገጠማቸዉን ተግዳሮት የሚመለከተዉ አካል እንዲቀርፍላቸው ጠይቀዋል፡፡ ኮሌጁ የጀመረዉ የግንባታ ሂደት መጓተት ከፍተኛ ቅሬታ እንደፈጠረባቸዉ ከአከባቢዉ ነዋሪዎች መካከል አስተያየት የሰጡት አቶ ፍስሃ ወልደሚካኤል ገልፀዋል፡፡ በወቅቱ ነዋሪዉ በቂ ዝግጅት እንኳን ሳያደርግ ለልማት ሲባል ራሱን ለአደጋ አጋልጦ የተነሳ ሲሆን ልማቱ በተፈለገዉ ልክ ሳይሄድ በዚህ መልክ መቆሙ የሚያሳዝን ነዉ ብለዋል፡፡   ድምጽ መግቢያ 2፡55 ''ይገነባል ተብሎ------- አላለቀም'' መውጫ 3፡39   እንደነዚህ ያሉ ተግባራት ለሃገርም ሆነ ለመንግስት ከሚያተርፉት ኪሳራ ባሻገር ህዝብና መንግስት እንዲቃቃር እያደረጉ ስለሆነ የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ መስጠት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡   የኮሌጁ ዲን አቶ ወንድሙ ዳዊት ኮሌጁ የጀመራቸው የመሰረተ-ልማት የማስፋፊያ ግንባታዎች በጊዜ አለመጠናቀቅ በመማር ማስተማር ውጤታማነት ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡   ድምጽ መግቢያ3፡49 ''አይታችሁ ከሆነ-------ተጽእኖ አለው'' መውጫ 5፡17   ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት አጥጋቢ ባይሆንም ያሉትን ክፍሎች ለእይታ ሳቢ እንዲሆኑ ማሳመርና ጥበቱን ለመቀነስ ከ20 በላይ የመማሪያ ክፍሎች የሚይዝ ህንጻ እየሰሩ መሆናቸዉን ገልፀዋል፡፡   በቀጣይ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የአከባቢዉ ማህበረሰብ፤ ባለሃብቶች፤ የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ሌሎችንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ኮሌጁ ያለበትን ደረጃ የሚገመግም የምክክር መድረክ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ መሆናቸዉን ነዉ አቶ ወንድሙ የገለጹት፡፡   ድምጽ 5፡27 ''ጥሩ የሆነ-------- ማለት ይቻላል'' መውጫ 6፡31   ከስምንት ዓመታት በፊት በ18 ወራት ግንባታዉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይዉላል በሚል ከ16 በላይ ነዋሪዎች በማስነሳት የማስፋፊያ ግንባታ መጀመሩን ያስታወሱት የወላይታ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ አቶ ዳዊት አበበ በበኩላቸዉ ቅሬታዉ አግባብ ነዉ ብለዋል፡፡   ድምጽ መግቢያ 6፡41 ''በማስፋፊያ----ችግር ፈጥሯል'' መውጫ 7፡45   ያለመጠናቀቁ መሠረታዊ ችግር ኮንትራክተሩ ጥሎ በመጥፋቱ የተፈጠረ ችግር መሆኑን ገልጸው በህጋዊ ሂደት በማረም ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡   ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላትም ሃላፊነታቸዉን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡   ድምጽ መግቢያ 8፡00 ''የግንባታ አለመጠናቀቅ----የእያደረገ ነው'' መውጫ 8፡49   ከተቋቋመ ከ20 ዓመት በላይ የሆነዉ የሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአሁኑ ሰዓት በመደበኛና መደበኛ ባለሆነ ኘሮግራም ከደረጃ አንድ እስከ አምስት ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ እንደሚገኝ ከኮሌጁ የተገኘዉ መረጃ ያሳያል፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም