በኢትዮጵያ የታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዘጠኝ የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ የታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዘጠኝ የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል
ኢዜአ ታህሳስ 22/2012 በኢትዮጵያ የታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሶስተኛ ቀን ውሎ ዘጠኝ የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል።
ሻምፒዮናው በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም ከታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን፤ በሶስተኛው ቀን ውሎ ዘጠኝ የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል።
ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ሁለት ሺህ ሜትር መሰናክል ሴቶች አትሌት መሰረት የሻነህ ከተንታ የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 6 ደቂቃ ከ40 ሴኮንድ ከ5 ማይክሮ ሴኮንድ አሸንፋለች።
የደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ተወዳዳሪ አትሌት ብዙነሽ ጌታሁን 6 ደቂቃ ከ48 ሴኮንድ ከ2 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ፣ አትሌት አለምፀሐይ መኩሪያው ከተንታ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 6 ደቂቃ ከ53 ሴኮንድ ከ3 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ ወጥታለች።
ከ18 ዓመት በታች ወንድ ሁለት ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ሀብታሙ ድሉ ከተንታ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 5 ደቂቃ ከ53 ሴኮንድ ከ4 ማይክሮ ሴኮንድ አሸናፊ ሆኗል።
አትሌት ተሾመ ወንድወሰን ከደብረብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 5 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ7 ሴኮንድ ሁለተኛ ደረጀ ዳጨው ከኦሮሚያ ክልል 6 ደቂቃ ከ2 ሴኮንድ ከ4 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ ወጥቷል።
ከ18 ዓመት በታች ሴት 1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት አለነሽ ባወቀ ከተንታ የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 4 ደቂቃ ከ32 ሴኮንድ ከ2 ሴኮንድ አሸንፋለች።
ሌላኛው የተንታ አትሌቲክስ ማዕከል ተወዳዳሪ አትሌት መሰረት እንዳው 4 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ ሴኮንድ ሁለተኛ በከሼ አላኒ ከኦሮሚያ ክልል 4 ደቂቃ ከ36 ሴኮንድ ከ 9 ሴኮንድ ሶስተኛ ወጥታለች።
ከ16 ዓመት በታች ሴት 100 ሜት አትሌት ጆክ ኦባንግ በ13 ሴኮንድ አሸናፊ ሲሆን አትሌት ጫልቱ ባናታ ከኦሮሚያ ክልል 13 ሴኮንድ ከ2 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ ወጥታለች።
የትግራይ ክልል ተወዳዳሪዋ ሄለን ሃይለማርያም 13 ሴኮንድ ከ 6 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን ይዛለች።
ከ16 ዓመት በታች ወንድ 100 ሜትር ሙሰአብ ሙከሚል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 11 ሴኮንድ ከ 5 ማይክሮ ሴኮንድ አሸናፊ ሲሆን አትሌት ቢኒያም አፅብሃ ከትግራይ ክልል 11 ሴኮንድ ከ 7 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ ወጥቷል።
አትሌት ቴዎድሮስ ይብራህ 11 ሴኮንድ ከ 9 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል።
ከ16 ዓመት በታች ወንድ ጦር ውርወራ አትሌት አብዱርከሪም ኑራ ከኦሮሚያ ክልል 57 ነጥብ 22 ሜትር በመወርወር አሸናፊ ሆኗል።
ሌላኛው የኦሮሚያ ክልል ተወዳዳሪ አትሌት ተሰማ ዱብሌ 45 ነጥብ 77 ሜትር በመወርወር ሁለተኛ፣ ልዑል በላይ ከትግራይ ክልል 35 ነጥብ 42 ሜትር በመወርወር ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
ከ18 ዓመት በታች ሴት 400 ሜትር መሰናክል አትሌት ነጻነት ወርቁ ከደብረብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 1 ደቂቃ ከ 10 ሴኮንድ ከ00 ማይክሮ ሴኮንድ አሸንፋለች።
አትሌት ሰብለ ጌታቸው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 1 ደቂቃ ከ15 ሴኮንድ ከ8 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ አትሌት አያት ጀማል ከኦሮሚያ ክልል 1 ደቂቃ ከ 17 ሴኮንድ ከ 2 ማይክሮ ሴኮንድ ሶስተኛ ወጥታለች።
ከ16 ዓመት በታች ሴት ስሉስ ዝላይ አትሌት ሂንሴኔ ተሰማ ከኦሮሚያ 10 ነጥብ 38 ሜትር በመዝለል አሸናፊ ስትሆን ኘሉዋክ ፖል ከጋምቤላ ክልል 10 ነጥብ 27 ሜትር በመዝለል ሁለተኛ ወጥታለች።
አትሌት ቦነተ ጫከኔ ከኦሮሚያ ክልል 9 ነጥብ 98 ሜትር ሶስተኛ ደረጃ ይዛ ውድድሯን አጠናቃለች።
ከ18 ዓመት በታች ወንድ ስሉስ ዝላይ አትሌት በረከት ማርቆስ ከኦሮሚያ ክልል 14 ነጥብ 20 ሜትር በመዝለል አሸንፏል።
አትሌት ተገኝ ፋሲካ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል 14 ነጥብ 9 ሜትር በመዝለል ሁለተኛ አትሌት ሳምሶን ቤከማ 13 ነጥብ 91 ሜትር በመዝለል ሶስተኛ ወጥቷል።
የኢትዮጵያ የታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገም ሲቀጥል ስድስት የፍጻሜና ሁለት የማጣሪያ ውድድሮች እንደሚካሄዱ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በሻምፒዮናው በሁለቱም ጾታዎች ከአማራ ክልል ውጪ ስምንቱ ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በተጨማሪም ከአማራ ክልል የደብረብርሃንና የተንታ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላትም የሚሳተፉ ሲሆን ወንድ 176 ሴት 148 በድምሩ 324 አትሌቶች በሻምፒዮናው እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ሻምፒዮናው ከ18 ዓመት በታችና ከ16 ዓመት በታች በሚል በሁለት የእድሜ ዘርፎች የሚካሄድ ነው።
ከ18 ዓመት በታች ላይ እድሜያቸው 16 እና 17 የሆኑ አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን ከ16 ዓመት በታች ላይ እድሜያቸው 15 የሆኑ አትሌቶች ይሳተፋሉ።
ሻምፒዮናው እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ይቆያል።