ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በፍንዳታው የተጎዱትን ሰዎች በመጎብኘት ላይ ናቸው

73
አዲስ አበባ ሰኔ 16/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ በዘውዲቱና ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች ተገኝተው በፍንዳታው የተጎዱትን ሰዎች በመጎብኘት ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ያመጡትን ለውጦች ለመደገፍና እውቅና ለመስጠት በዛሬው ዕለት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በመስቀል አዳባባይ ሰልፍ አድርገዋል። በዚሁ ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት በኋላ በደረሰው የቦንብ ፊንዳታ በንጹኃን ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉም ተገልጿል። የተጎዱት ሰዎች ወደ ዘውዲቱ፣ አቤት፣ ምኒልክና ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች ተወስደው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በሆስፒታሎቹ በመገኛት ጉዳተኞቹን በመጎብኘት ላይ ናቸው።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም