ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ጅማ አባጅፋር ተጋጣሚውን ቅድስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

ኢዜአ ታህሳስ 18/2012 በአምስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ጅማ አባጅፋር ተጋጣሚውን ቅድስ ጊዮርጊስን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡ የማሸነፊያውን ጎል ባለፉት አራት ጨዋታዎች በጉዳት ያልተሰለፈው ብዙአየው እንደሻው ጨዋታው በተጀመረ በ13 ደቂቃ በማስቆጠር ባለሜዳዎችን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ተጠናክረው የገቡት ቅድስ ጊዮርጊሶች ተደጋጋሚ የጎል ሙከራ ካደረጉ በኃላ አቻ መሆን የቻሉበትን ጎል በቅድሞ በጅማ አባጃፋር ተጫዋች በሄኖክ አዱኛ በስልሳኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጥር ችለዋል፡፡ ጅማ አባጀፋሮች ጨዋታውን ሊጠናቀቅ ሲቃረብ ያደረጉት የማጥቃት እርብርብ ተቀይሮ በገባው በአምረላ ደቻሳ አማካኝነት በሜዳቸው የማሸናፊቸውን ጎል በማስቆጠር ነጥባቸውን ወደ ስድስት ከፍ ማድረግ ችለዋል፡፡ ቅድስ ጎርጊስ ከመሸነፋቸው ጋር ተያይዞ በነበረበት ስድስት ነጥብ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡ ጅማ አባጃፋር የዛሬውን ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲሱ ጅማ ዩኒቨርስቲ ስፖርት አካዳሚ ስታዲየም አካሂዷል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም  በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የወልቂጤ ከነማ አቻውን በሜዳው ያስተናገደው ወላይታ ድቻ አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት ተሸንፋል። በሌላ በኩል ሀድያ ሆሳዕና ከባህር ዳር ከተማ ሁለት ለሁለት በሆነ ውጤት መጠናቀቁን ከስፍራው ሪፖርተሮቻችን ዘግበዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም