ቀጥታ፡

መገናኛ ብዙሃን ለመጪው ምርጫ አስቀድመው ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል ተባለ

ኢዜአ ታህሳስ 18/2012.. የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በዚህ ዓመት ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው አገር አቀፍ ምርጫ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ተገለፀ። ምርጫውን ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያዩ ዝግጅቶችን እያደረጉ መሆኑን ይገልጻሉ። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ ባለሙያዎች ህዝቡ ስለምርጫው ትክክለኛ፣ ሚዛናዊና ተገቢ መረጃ በመያዝ የበኩሉን ውሳኔ ይሰጥ ዘንድ የመገናኛ ብዙሃን ሚና የላቀ መሆኑን ገልፀዋል። በመሆኑም ይህንን ሚናቸውን ለመወጣት የሚያስችላቸውን ዝግጅት ከወዲሁ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ሰሉ አሳስበዋል። እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ገለጻ የምርጫ ዘገባ ከሌሎች ዘገባዎች በተለየ ከፍተኛ ጥንቃቄን ይሻል። የመገናኛ ብዙሃን የምርጫውን አጠቃላይ ዝግጅት ጨምሮ እስከ ድምፅ መስጠትና ቆጠራ እንዲሁም ውጤት መግለፅ ድረስ ያለውን ሂደት ሲዘግቡ እጅግ የላቀ ኃላፊነትና ጥንቃቄን ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል። የመገናኛ ብዙሃን መጪውን ምርጫ በተመለከተ ትክክለኛና ሚዛናዊ ዘገባዎችን ማቅረብ በሚቻልበት መንገድ መነጋገርና ጥንቃቄ የተሞላበት እቅድ ማዘጋጀት አለባቸው ሲሉ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለኢዜአ ተናግረዋል። ምርጫውን በተመለከተ የሚመሩበት መተዳደሪያ ደንብ ጭምር በመቅረፅ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ፈተናዎችን እንዴት ማለፍ ይቻላል በሚሉና መሰል ሁኔታዎች ዙሪያ ከወዲሁ በመነጋገር ስልት እንዲዘይዱ መክረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህርት ዶክተር አጋረደች ጀማነህ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ስለ ምርጫና የምርጫ ሂደቶች ጠንቀቀው ማወቅና በቅድመ ምርጫና በድህረ ምርጫ ምን አይነት ዘገባዎች እንደሚያቀርቡ ከወዲሁ ለባለሙያዎች ስልጠና ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። በተለይ ህዝቡ ውስጥ ግርታ የሚፈጥሩ ጉዳዮችን ከማቅረብ መቆጠብና ህዝቡ የሚመርጠውን ፓርቲ አጀንዳ በአግባቡ እንዲገነዘብ ግልጽ መረጃ የማቅረብ ሃላፊነት እንዳለባቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የዘንድሮውን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል። በቅርቡም አጠቃላይ የምርጫ ሰሌዳ ይፋ ያደርጋል ተብሎም ይጠበቃ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም