ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ጅማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ገብተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ጅማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ገብተዋል
ኢዜአ ታህሳስ 18/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የመረዋ - ሶሞዶ - ሰቃ - ሲሞዶ - ሊሙ መንገድ ግንባታን ለማስጀመር ዛሬ ጧት ጅማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ገብተዋል።
94 ኪሎሜትር ርዝመት የሚሸፍነው ይህ የመንገድ ግንባታ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።
ለመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚደረግ ሲሆን የቁጥጥር ስራውን ጨምሮ ሙሉ ወጪው በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ይሆናል።
በመንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።