ቀጥታ፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ክስ ተመሰረተባቸው

ኢዜአ ታህሳስ 17/2012 የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ  ኢንጂነር አዜብ አስናቀ ክስ ተመሰረተባቸው ። በዚህ የክስ መዝገብ የቀድሞ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር  ኮሎኔል ሙሉ ወልደገብርኤልን ጨምሮ 50 ሰዎች ይገኙበታል።

ክሱ የተመሰረተው ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ተያይዞ በተካሄደ የደን ምንጣሮ ስራ ጋር ተያይዞ ነው።

ኢንጂነር አዜብ አስናቀ በነሐሴ ወር 2010 ዓ.ም ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም