በካዛኪስታን 98 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ተከሰከሰ - ኢዜአ አማርኛ
በካዛኪስታን 98 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ተከሰከሰ
ኢዜአ፤ ታህሳስ 17/2012 98 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ካዛኪስታን ውስጥ ተከሰከሰ ንብረትነቱ የቤክ ኤይር አየር መንገድ የሆነው ፎከር 100 የተሰኘው አውሮፕላን ካዛኪስታን አልማቲ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ተከስክሶ እስካሁን በትንሹ 14 ሰዎች ሞተዋል። ባለሁለት ወለለል ህንጻ ላይ በተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ ከነበሩት ውስጥ 93 መንገደኞች እና አምስት የበረራ ሰራተኞች መሆናቸውም ታውቋል።
የአውሮፕላን ማረፊያው ባለስልጣናት እንዳሉት አውሮፕላኑ ከአልማቲ ወደ ኑር ሱልጣን ከተማ ለመጓዝ በረራ እንደጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ልዩነት ነው የተከሰከሰው። ህጻናትን ጨምሮ ጉዳት የደረሰባቸው ከ60 የማያንሱ ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። የአውሮፕላን አደጋው ምክንያት እስካሁን አልታወቀም ሲል ቢቢሲ በድረገጹ አስነብበል።