ቀጥታ፡

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15/ 2012 የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዚዳንቱ ለሁለት አስርት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ከታደሰ በኋላ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። በአሁኑ ጉብኝታቸውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም